Category Archives: News

Overview News

በሼር ኢትዮጵያ እስታዲየም ሲካሄድ የነበረው ጨዋታ ተጠናቀቀ

31 May 2023 Aswin Endeman
በሼር ኢትዮጵያ እስታዲየም ሲካሄድ የነበረው ጨዋታ ተጠናቀቀ

በኢትዮጵያ የግር ኳስ ፌደሬሽን አመራርነት ከተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች ተዉጣጥተው በምድብ C  ተከፍለዉ ወደ ሼር ኢትዮጵያ እስታዲየም ተልከዉ የነበሩ 13 ቡድኖች ለተከታታይ ሁለት ወራት ሲያካሂዱ የነበረዉን የስልጠና እና የጨዋታ መርሃግብር  ያለምንም  የእስታዲየም ወጪ አጠናቀው ባሳለፍነው ሳምንት ወደ መጡበት ተመልሰዋል፡፡

በፍፃሜው ጨዋታም የካ ክፍለ ከተማ ከአዲስ አበባ እና ሀበሪቾ ከደቡብ ክልል ሀዲያ ዞን ተጋጥመው  ሀበሪቾ 1-0 አሸንፏል። አሸናፊዎቹን እንኳን ደስ አላችሁ እያልን በስታዲየማችን በርካታ ተመልካቾች እና ደጋፊዎቻቸው ብዙ አጓጊ ጨዋታዎችን በመመልከት  በመቻላቸው ደስተኞች ነን።

ሼር ኢትዮጵያ ለመረሃግብሩ መሳካት ሲያበረክት ለነበረዉ አስተዋፅኦ በፌደሬሽኑ እና በስፖርት ማህበረሰቡ ግንዛቤ ውስጥ በመግባቱና ይህንንም ማረጋገጥ ያስቸል ዘንድ የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል፡፡

Overview News

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጉብኝት

24 May 2023 Aswin Endeman
Hawassa University students visiting

ቅዳሜ ግንቦት 12 /2015 ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተጋበዙ የሆርቲካልቸር እና የዕፅዋት ሳይንስ ተማሪዎችን እንዲሁም መምህራንን አስተናግደናል። አቀባበል ከተደረገላቸዉም በኋላ ስለ እርሻዉ እንቅስቃሴ አጭር መግቢያ ተሰጥቷል በዚህም ላይ የኩባንያው CSR ተግባራትም ተብራርተዋል. በመቀጠልም የግሪን ሃውስ፣ የደረጃ አሰጣጥ፣ የዌት ላንድ እና  የመስክ ጉብኝት ተካሂዷል።

ኩባንያው አካባቢያዊ እና ማህበራዊ መስተጋብሩን ተግባራዊ በሆነ መልኩ ለማሳየት ጥሩ አጋጣሚ የፈጠረለት ነበር፡፡. በመጨረሻም ተሳታፊዎቹ ሼር ኢትዮጵያ በማህበራዊ አገልግሎትና በአካባቢ ጥበቃ ላይ እያስመዘገበ ያለው ልማት እንዳስደነቃቸው ገልፀዋል።

እነዚህ ተማሪዎች በኢትዮጵያ በአበባ፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ዘርፍ ብሩህ ተስፋን ለመገንባት ትልቅ ሚና እንደሚጫወቱ ተስፋ እያደረግን ይህንን ዝግጅት በማቀዱና በማዘጋጀቱ EHPEAን እናመሰግናለን።

Overview News

በቦረና ዞን በድርቅ ለተጎድ ማህበረሰቦች የሚውል የምግብ እርዳታ

14 April 2023 Aswin Endeman
በቦረና ዞን በድርቅ ለተጎድ ማህበረሰቦች የሚውል የምግብ እርዳታ sher

ባለፈው አመት በቦረና ዞን ድርቅ ተከስቶ ለሰብል ውድመት እና ለከብቶች ሞት ምክንያት ሆኗል ። ይህም በዘንድሮው አመትም በድጋሚ በመከሰቱ  ህዝቡን ለመደገፍ ሀገር አቀፍ ዘመቻ ተጀምሯል። ሼር ኢትዮጵያም ዘመቻውን በመቀላቀል  13 ቶን የበቆሎ ዱቄት ገዝቶ ፣ አርብ  መጋቢት 29  ለባቱ/ዝዋይ  ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት   እና የተወሰኑ ሌሎች አመራሮች  በተገኙበት ርክክብ ተፈጽሟል ። እነሱም የተረክቡትነ የምግብ እህል በወቅቱ ለተጠቃሚዎች እንደሚያደርሱ ቃል ገብተዋል።

 

 

 

Overview News

የአለም አቀፍ የሴቶች ቀን አከባበር በሩዋንዳ

4 April 2023 Aswin Endeman
የአለም አቀፍ የሴቶች ቀን አከባበር በሩዋንዳ

ከመጋቢት 12__15 / 2015 በፌርትሬድ የተመዘገቡ እርሻዎች ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በዱኩንዴ ካዋ ሙሳሳ የቡና እርሻ በኪጋሊ ሩዋንዳ አንድ ላይ አክብረዋል። ተሳታፊዎቹ ከኬንያ፣ ታንዛኒያ፣ ኮንጎ፣ ኡጋንዳ እና ኢትዮጵያ የተውጣጡ ነበሩ። ሼር ኤትዮጵያን በመወከልም ወ/ት ሕሊና ደበበ መኮንን የመረሃ ግብሩ ተሳታፊ ነበረች ።

ቡድኑ እንደ ዱኩንዴ ካዋ ሙሳሳ ኪጋሊ አቅራቢያ የሚገኘውን የቡና እርሻ የመሳሰሉ በርካታ ኩባኛዎችን ጎብኝቷል። እ.ኢ.አ በ2003  የተመሰረተው ይህ ኮፕሬቲፍ ከ300 ቡና አብቃይ ገበሬዎች ወደ 2,000 በላይ አድጓል። ሰማንያ በመቶው የዱኩንዴ ካዋ አባላት ሴቶች ሲሆኑ። ቡናቸውንም ”በሴቶች የመረተ ቡና ” ብለው ለገበያ ያቀርባሉ። ፌርትራድ ፕሪሚየም በመጠቀም ለህፃናት ትምህርት እና ማህበረሰቡን በቀጥታ የሚደግፉ ፕሮጀክቶችን ለምሳሌ እንደ ልብስ ስፌት ያሉ ለአካባቢው ገበያ እንደገና ጥቅም ላይ የሚውሉ የንፅህና መጠበቂያ ፓድዎችን የሚያመርት ነው። በካጄራ የህብረት ስራ ዩኒየን ሴቶችና ወጣቶች በሳሙና አመራረት እና በንብ ማነብ ላይ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል።

በእርሻችን እና በማህበረሰባችን ውስጥ የሴቶችን ሚና እና አቋም ማስከበር ለተለያዩ እና አካታች የሰው ሃይል በምናደርገው ጥረት ወሳኝ ግብ ነው። ለሰራተኞቻችን እና ለእዚህ አላማ አስተዋፅኦ ለሚያደርጉ የማህበረሰብ አባላት የተለያዩ ፕሮግራሞችን እና የስልጠና ኮርሶችን መስጠቱን እንቀጥላለን፣ በአለምአቀፍ ሁኔታ ከሌሎች እርሻዎች ለመማር እድል ስለሰጠን ፌርትሬድን ልናመሰግነው እንፈልጋለን በማለት ፕሮግራማቸውን አጠናቀዋል።

           

Overview News

ባርንሆርን ስኮላርሺፕ ለሌላ አራት ተማሪዎች ተሰጠ

20 March 2023 Aswin Endeman
Awarded Barnhorn Scholarships to 4 students

በቅርቡ ለሁለተኛ ዙር ጌሪት እና ኔል ባርንሆርን ስኮላርሺፕ ለአራት የሼር-ትምህርት ቤት ተማሪዎቸ ተሰጥቷል። የባርንሆርን ቤተሰብ ሼር ኢትዮጵያ  እርሻን ፣ ሆስፒታል ና ትምህርት ቤቶቹን የመሰረቱ ናቸው። በየአመቱ ለ4 ተማሪዎች በኢትዮጵያ በመረጡት ዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት ወጪን እና የኑሮ ውድነት ለመደገፈ ብሎም ለመሸፈን የሚረዳ ወርሃዊ ገንዘብ ይሰጣቸዋል። የስኮላርሺፑ ዋና ግብ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡና  የተቸገሩ ተማሪዎችን ለመርዳት ያስበ ነው።

ተማሪዎቹም ጣሃ አቡ ጁላ፣ ተመስገን ሰለሞን ስጦታ፣ ደጀኔ ኢጃሮ ናኔሶ እና ሃና በላይሁን ድልነሳው ሲባሉ ሽልማታቸውን ከጌሪት እና ኔል ባርንሆርን ልጅ ከጆን ባርንሆርን እጅ ተቀብለዋል። ጆን ባርንሆርም ተማሪዎቹ ላለፉት 16 ዓመታት ላሳዩት ትጋት  እና እንዲሁም የሼር ትምህርት ቤት መምህራንና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን በተማሪዉ ቤተሰብ ስም አመስግኗል።

ከሁሉም 12 ከፍል ካጠናቀቁ ተማሪዎቸ ዉስጥ 8 ተማሪዎች  ለስኮላርሺፕ  ታጭተው 4ቱ በመጭረሻዉ ማጣሪያ ተመርጠዋል። ሌሎቹ 4 ቶቹ ድገሞ  እያነዳነዳችዉ የላፕቶፕ ሽልማት አግኝተዋል። ስነ ስርዓቱም የተማሪ ቤተሰቦች፣የሼር ኢትዮጵያ ስራ አስኪያጆች፣የማህበረሰብ ሽማግሌዎች፣የሼር ት/ቤት ሰራተኞች፣የወላጆች ኮሚቴ እና የትምህርት ጽ/ቤት  አስተዳደሮች ፣ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በሼር ት/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ  ተካሂዷል።

አቶ  ባርንሆርን እና ቤተሰባችው ባለፉት አመታት ለሼር ትምህርት ቤቶች እና ሆስፒታል ያላሰለሰ ድጋፍ ስላደረጉልን እያመሰገንን እነዚህ ተማሪዎች ሼር ኢትዮጵያ በዝዋይ እና አካባቢው ማህበረሰብ ላይ እያሳደረ ያለው አዎንታዊ ተጽእኖ እውነተኛ ምሳሌ መሆናቸው ለመግለፅ እንወዳልን። ሁሉም የ12ኛ ከፍል ፈተናን ላጠናቀቁ ተማሪዎቸ እንዲሁም በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎቸ ለተመደባቸዉ ተማሪዎች  መልካም የተምህርት ጊዜን እንመኘላችሃልን።

በኢትዮጵያ የሚገኙ የሼር ትምህርት ቤቶች ከ6800 በላይ ተማሪዎችን በሶስት ቦታዎች ያስተምራሉ። ወደ 400 የሚጠጉ ህጻናት – ከ 4 አመት ጀምሮ – በየዓመቱ በሼር ትምህርት ቤቶች ምዝገባ ወይም ቅበላ የሚከናወን ሲሆን ይህም 50 %  ከአካባቢው ማህበረሰብ  ልጆች  እና 50% ቱ ድገሞ ከሠራተኞች ልጆች  ይሆናለ።

Overview News

ሆርቲፍሎራ ኤክስፖ

17 March 2023 Aswin Endeman
Hortiflora expo

ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ በተካሄደው 8ኛው የሆርቲፍሎራ ኤግዚቢሽን ላይ ሶስት አስደሳች  ቀናትን በታላቅ ደስታ መለስ ብለን ሰንመለከት፣ ኤግዚቢሽኑ የተከፈተዉ በግብርና ሚኒስትሩ ዶ/ር ግርማ አመንቴ ሲሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።

ለእኛ ኤግዚቢሽኑ ከብዙ  ፍላጎት ካላቸው አካላት ጋር ስለ እርሻዎቻችን እና ውብ ጽጌረዳዎቻችንን በዘላቂነት ስለምናመርትበት መንገድ ለመነጋገር ጥሩ አጋጣሚ የፈጠረ ነበር። ብሎም ስለ ብዙው የCSR ፕሮጄክቶቻችንና፣ የእንቦጭ አረምን ከሀይቁ ላይ ለማሰወገድ በሚደረገው ዘመቻ የአካባቢውን ሴቶች በማስልጠን የተለያዪ ዓይነት የእጅ ስራ ምርቶችን አረሙን በመጠቀም አምርተዉ ለገበያ እንዲያቀርቡ በማድረግ  የምናበረከተውን አስተዋጽኦ  ጨምሮ ለመግልጽ ችለናለ፡፡

በዚህ አመት የኤግዚቢሽኑ መሪ ቃሉ ዘላቂነትን ማረጋገጥ’ የሚል ነበር እና ከEHPEA  (Gold certificate Code of Conduct) and MPS (Hortifoot print Calculator) የተባሉ  ሽልማቶችንም በማግኘታቸን  እንኮራለን።

በአጠቃላይ የተሳካ  ኤግዚቢሽን ነበር  እና ሁሉንም ጎብኝዎቻችንን በዚሁ እጋጣሚ ለማመሰገን እንውዳለን።

Overview News

በአዳሚ ቱሉ ሼር አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አዲስ የዉሃ ጉድጓድ

24 February 2023 Aswin Endeman
New borehole for Sher Elementary School in Adami Tulu

ባለፈው ሳምንት በአዳሚ ቱሉ በሚገኘው የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤታችን የዉሃ ጉድጓድ ተቆፍሮ ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ዓመት 4 የመመሪያ ክፈሎች ግንባታ እንጀምራለን፡፡ ይህ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሼር መዋላ ህፃናት ትምህርት ቤት በጣም ቅርብ ነው። መዋለ ህፃናት አሁን 350 ተማሪዎች አሉት። ለአዲሱ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዝግጅት ተጀምሯል። የተጀመረዉ ከውሃ እና ኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ነዉ፡፡ ውሃ በ 77 ሜትር ጥልቀት ላይ ወጥቷል. ምስጋናችን ለክርስቲያን ሰርቪስ ኢንተርናሽናል; ትምህርት ቤቶቻችን በሚገኙባቸው ቦታዎች ሁሉ የውሃ አቅርቦትን ለማሻሻል እየረዱን ነዉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ዛፎችን እና ተክሎችን ለማጠጣት እና መጸዳጃ ቤቶችን ለማጠብ በቂ ውሃ አለን:: የጉድጓድ ውሃ በቧንቧ በኩል ለአካባቢው ማህበረሰብ አባላት በነፃ እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡ አዲሱ የሼር አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መገንባት በትምህርት፣ በስራ እድል እና በመሠረተ ልማት ብዙ የሚፈለገውን እድገት ያመጣል።

Overview News

ሼር ተማሪዎች ተሸለሙ

31 January 2023 Aswin Endeman
Sher students awarded

በቅርቡ ከ8ኛ ክፍል ተማሪዎቻችን ሶስቱ በተለየ ችሎታ ግኝት እና በፈጠራ ውድድር ላይ ተሳትፈዋል፤ የተለየ ፈጠራ የተዘጋጀዉ በኦሮሚያ ትምህርት ጽ/ቤት ነዉ፡፡ ውድድሩ በክልል ደረጃ የነበረ ሲሆን “በኦሮሚያ ሴት ተማሪዎች ቀን”  ላይ ቀርቧል፡፡ ይህም ዝግጅት በአዲስ አበባ በኦሮሚያ ባህል ማዕከል ተካሄዷል።

በእጅ ጥበብ ዘርፍ ሄለን ዮሴፍ፣ ማህሌት ብርሃኑ እና ቀነኒቱ ተሾመ አሸናፊ ሆነዋል፡፡ እነሱም ሜዳሊያዎችን እና የምስክር ወረቀት አግኝተዋል፡፡ በእለቱ የጥበብ ስራዎቻቸውን በታዳሚ ፊት እንዲያቀርቡ እድል የተሰጣቸዉ ሲሆን በመምህር ሮቢቲ መንገሻ ታጅበው ነበር፡፡ በዓሉን ለማክበር በማግስቱ የወዳጅነት ፓርክን ለማየት ሄደዋል፡፡

ወደ ሼር ትምህር ቤት ከተመለሱ በኋላም ሴት ልጆች በትምህርት ቤቱ አስተዳደር እና በተማሪዎቻቸው የክብር አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ ሴት ልጆቻችን ጥሩ  ስራ ሰርተዋል፡፡

 

Overview News

አዲስ የስራ ማስታወቂያ፡ ፀሐፊ/ የአስተዳደር ረዳት

27 January 2023 Aswin Endeman

በአዲስ አበባ ለሚገኘዉ ጽ/ቤታችን ወጣትና የመስራት አቅም ያላት፣ እንግሊዝኛ ቋንቋን አቃልጥፋ የምትናገር ከዉጭ የማስመጣት ሂደትን የምትከታተል እና የየእለቱን የፀሐፊነት ስራ ኃላፊነት የምትወጣ ፀሐፊ/የአስተዳደር ረዳት መቅጠር እንፈልጋለን፡፡

Please click here to find more information.

 

 

Overview News

ሸር ትምህርት ቤት የአካባቢ ፅዳት ቀን

10 January 2023 Aswin Endeman
Guyyaa Qulqullinaa Naannoo Mana Barumsaa Sheeri

የሸር ትምህርት ቤት ተማሪዎች በዛሬው ቀን የትምህርት ቤታችውን አካባቢ በማፅዳት አኩርተውናል፡፡ ይህ የፅዳት ስራ በአካባቢ ጥበቃ ክለብ አስተባባሪነት፤ በአስተማሪዎች እና በተማሪዎቻችን በጎ ፍቃድ የፕላስቲክ እና የተለያዩ ደረቅ ቆሻሻ ለመሰብሰብ ተችሏል፡፡ እንደሚታወቀው እንደ ሀገር የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ስርዓታችን የተሸሻለ  አይደለም፡፡ አስተማሪዎች እና ተማሪዎቻችን ለመጭው ትውልድ የፀዳ አካባቢን ለመፍጠር መነሳሳታቸውን አሳይተውናል፡፡ ጥሩ ስራ ተማሪዎቻችን!