Category Archives: News

Overview News

መላ ለእሷ፡ ለወጣት ሴት ልጃገረዶች ዘላቂ በሆነ የወር አበባ መፍትሄ

5 December 2022 Aswin Endeman

ባሳለፍነው ሳምንትበሼር-ትምህርት ቤታችን ለሚገኙ ለ1300 ሴት ተማሪዎች ፡ መላ ለሷ የሚል መጠሪያ ያለው አዲስ ፕሮጀክት ጀምረናል። የፕሮጀክቱ መጠሪያም እንዲሆን የመረጥነው (መላ)የአማርኛ ትርጓሜያዊ ፍች መፍትሄ የሚል ትርጉም ኣለው። በአፍሪካ ውስጥ ለሚገኙ ለብዙ ወጣት ሴቶች እና ልጃገረዶችችግር የሆነውን በዋጋ ተመጣጣኝ የሆነየሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ምርቶች እጥረትየሚቀርፍ መፍትሄ ነው:

ለብዙ ሰዎች የወር አበባ ንፅህና ጥበቃ ምቹ አይደለም። በዓለም ለሚገኙ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ልጃገረዶች ደግሞ በትምህርት፣ በጤና፣ በራስ መተማመን እና በሰብዓዊ መብቶቻቸው ላይ እንቅፋት ይፈጥራል። ለሌሎች ብዙዎች ደግሞ የወር አበባ መጀመር ለትምህርትመስተጓጎል ምክንያት ሲሆን ይታያል።

መላ ለእሷ፥ለአካባቢ ተስማሚ እና ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ የወር አበባ ምርቶችን እና የወር አበባ ጤና አጠባበቅ ትምህርትን በመስጠት፣ የሴቶችን እና የልጃገረዶችን ህይወት ለመለወጥ ወጥኖ የተነሳ ኢትዮጵያዊ ማህበራዊ ድርጅት ነው። የሼር ትምህርት ቤቶች እና መላ ለእሷትብብር እና በኔዘርላንድ የአበባ ፋውንዴሽን እርዳታ እድሜያቸው ከ11 እስከ 18 ዓመት ላሉ 1300 ልጃገረዶች፥የወር አበባ ንፅህና መጠበቂያዎችን እርዳታ እናቀርባለን። ከንፅህና መጠበቂያዎቹ በተጨማሪ የባለሙያዎች ቡድን የሼር ትምህርት ቤት መምህራንን የሚያሰለጥን ሲሆን፣ ለ1300 ተማሪዎች ደግሞ በሴቶች ክበብ በኩል የወር አበባ ጤና አጠባበቅ ላይ ስልጠና ይሰጣል።

የመላለእሷ ቡድን ላደረጉት ትብብር ትልቅ የሆነ ምስጋና እናቀርባለን ፥በመቀጠል የሆላንድ አበባ ፋውንዴሽን ለዚህ ተግባር ላደረጉት ድጋፍ እና ለወደፊትምለዚህ ፕሮጀክት ቀጣይነት ያለው ድጋፍለማድረግ ላሳዩት ቁርጠኝነት ከልብ እናመሰግናለን። ወጣት ሴቶች እምቅ ችሎታቸውን እንዲጠቀሙ ክብራቸው የሚጠበቅበት መብታቸውንም የማይጣስበት ዓለም አንድ ላይ እንገንባ።

Overview News

መላ ለእሷ፡ ለወጣት ሴት ልጃገረዶች ዘላቂ በሆነ የወር አበባ መፍትሄ

3 December 2022 Aswin Endeman

ባሳለፍነው ሳምንት በሸር-ትምህርት ቤታችን ለሚገኙ ለ1300 ሴት ተማሪዎች ፡ መላ ለሷ የሚል መጠሪያ ያለው አዲስ ፕሮጀክት ጀምረናል። የፕሮጀክቱ መጠሪያም እንዲሆን የመረጥነው (መላ) የአማርኛ ትርጓሜያዊ ፍች መፍትሄ የሚል ትርጉም ኣለው። በአፍሪካ ውስጥ ለሚገኙ ለብዙ ወጣት ሴቶች እና ልጃገረዶች ችግር የሆነውን በዋጋ ተመጣጣኝ የሆነ የሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ምርቶች እጥረት የሚቀርፍ መፍትሄ ነው:

ለብዙ ሰዎች የወር አበባ ንፅህና ጥበቃ ምቹ አይደለም።  በዓለም ለሚገኙ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ልጃገረዶች ደግሞ በትምህርት፣ በጤና፣ በራስ መተማመን እና በሰብዓዊ መብቶቻችው ላይ እንቅፋት ይፈጥራል። ለሌሎች ብዙዎች ደግሞ የወር አበባ መጀመር ለትምህርት መስተጓጎል መክኒያት ሲሆን ይታያል።

መላ ለእሷ፥ ለአካባቢ ተስማሚ እና ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ የወር አበባ ምርቶችን እና የወር አበባ ጤና አጠባበቅ ትምህርትን በመስጠት፣ የሴቶችን እና የልጃገረዶችን ህይወት ለመለወጥ ወጥኖ የተነሳ ኢትዮጵያዊ ማህበራዊ ድርጅት ነው። የሼር ትምህርት ቤቶች እና መላ ለእሷ ትብብር እና በኔዘርላንድ የአበባ ፋውንዴሽን እርዳታ እድሜቸው ከ11 እስከ 18 ዓመት ላሉ 1300 ልጃገረዶች፥ የወር አበባ ንፅህና መጠበቂያዎችን እርዳታ እናቀርባለን። ከንፅህና መጠበቂያዎቹ በተጨማሪ የባለሙያዎች ቡድን የሼር ትምህርት ቤት መምህራንን የሚያሰለጥን ሲሆን፣ ለ1300 ተማሪዎች ደግሞ በሴቶች ክበብ በኩል የወር አበባ ጤና አጠባበቅ ላይ ስልጠና ይሰጣል።

የመላ ለእሷ ቡድን ላደረጉት ትብብር ትልቅ የሆነ ምስጋና እናቀርባለን ፥ በመቀጠል የሆላንድ አበባ ፋውንዴሽን ለዚህ ተግባር ላደረጉት ድጋፍ እና ለወደፊትም ለዚህ ፕሮጀክት ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ለማድረግ ላሳዩት ቁርጠኝነት ከልብ እናመሰግናለን። ወጣት ሴቶች እምቅ ችሎታቸውን እንዲጠቀሙ ክብራቸው የሚጠበቅበት መብታቸውንም የማይጣስበት ዓለም አንድ ላይ እንገንባ።

Overview News

መቅጠር ይፈልጋል።

9 November 2022 Aswin Endeman

የሼር ኢትዮጵያ ት/ቤት  የአንደኛ  እና  የሁለተኛ ደረጃ በተለያዩ ትምህርት አይነቶች ሁለት መምህራንን   መቅጠር ይፈልጋል።

ፍላጎት ያላችሁ ተወዳዳሪዎች በኢትዮ ጆብስ Ethio Jobs ድረገጽ በመግባት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

Overview News

አፍሪፍሎራ ሼር ፣ ቫን ዲጅክ ፍሎራ እና የኔዘርላንድ ፍላወር ፋውንዴሽን በጋራ በመሆን ለሼር ኢትዮጵያ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ወተት /እርጓ /የመመገብ ፕሮጀክትን አስጀመሩ።

26 October 2022 Aswin Endeman

ፕሮጀክቱም በዚህ የትምህርት ዘመን እድሜያቸዉ ከ4 እስከ 6 ዓመት የሚሆናቸው 1350 የሚሆኑ የሼር ኢትዮጲያ ትምህርት ቤቶች  ተማሪዎች በሳምንት ሁለት ጊዜ በጤናማ ንጥረ ነገሮች የበለጸገ የፕሮቲን እርጎ እንዲያገኙ ይረዳል። በአንድ ጊዜ የወተት ምገባ ለ አንድ የ5 አመት ልጅ ዕለታዊ የፕሮቲን ፍላጎት 33% እና 10% የቀን ካሎሪ ይሰጠዋል. እርጎው በየእለቱ ሁሉም ልጆች በትምህርት ቤት በሚያገኙት ትኩስ ምግብ ጋር አብሮ ይሰጣል ።

በፕሮጀክቱም ድጋፍ ልጆቹ የሚያስፈልጋቸውን የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ ያግዛል። በዚህ መንገድ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ስጋትን በመቀነስ የህጻናትን ትምህርት ተሳትፎ እንጨምር እናደርጋለን። ይህም ፕሮጀክት ከአስራ ስድስት ላላነሱ ሰዎች የሥራ እድል የሚሰጥ ሲሆን እንዲሁም ከሁለት በባቱ/ ዝዋይ / ውስጥ ከሚገኙ የወተት ተዋጽኦ አምራችና አቅራቢ ድርጅቶች ጋር የስራ ዉል ተፈራርመናል።

ከአጋሮቻችን ቫን ዲጅክ ፍሎራ እና የኔዘርላንድ ፍላወር ፋውንዴሽን ላደረጉልን ለዚህ ለጋስ እርዳታ በሁሉም የሼር ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች፣ ወላጆች እና አስተማሪዎች ስም እጅጉን የላቀ ምስጋና ልናቀርብላቸዉ እንወዳለን።

Overview News

ሼር ኢትዮጵያ ሆስፒታል አዲስ የማደንዘዣ መስጫማሽን ግዢ አከናወነ፡፡

25 October 2022 Aswin Endeman

በባቱ/ዝዋይ ከተማ የሚገኘው ሼር ኢትዮጵያ  ሆስፒታል አገልግሎቱን ለማሻሻል ባደረግነው ጥረት በቅርቡ አዲስ የማደንዘዣ መስጫማሽን ግዢ አከናዉኗል። የማደንዘዣ ሰጪ ባለሙያ የሆኑት ሲስተር ወርቄ አቦይ በሰጡት አስተያየት በማሽኑ አንድ ጊዜ ማደንዘዣዉን ለበሽተኛዉ ከተሰጠ በኃላ ሙሉ በሙሉ በራሱ  የሚሰራ በመሆኑ የማደንዘዣ ሰጪ ባለሙያዉ በሽተኛውን እየተከታተለ በቀዶ ጥገናው ስራ ላይ ተጨማሪ እርዳታን መስጠት ያስችለዋል ብለዋል።

ሌላው የአዲሱ ማሽን ጥቅም ደግሞ የሕፃናትን የቀዶ ጥገና ሕክምና  መስጠት የሚያስችል  መሆኑን የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ደምሳቸዉ ጌታቸዉ እንዲህ ሲሉ አብራርተዋል፡- ‘ከዚህ ቀደም ህጻናት ቀዶ ጥገና ሲያሰፈልጋቸዉ ወደ ሌሎች ሆስፒታሎች  የምንልክ የነበረ ሲሆን አሁን ግን አዲሱን ማሽን በመጠቀም ህክምናዉን በዚሁ በራሳችን ሆስፒታል መስጠት እንድንችል ያደርገናል ብለዋል፡፡

ማሽኑም በክፍሉ ከተተከለ እና  ለሚመለከታቸው ሁሉም የክፍሉ ሰራተኞች በአምራች ድርጅቱ ባለሙየዎች  ሙያዊ ስልጠና, ከተሰጠ በኃላ ሙሉ በሙሉ በስራ ላይ ይውሏል ፡፡

በሼር ኢትዮጵያ ሆስፒታል ሁሉም የሼር ሰራተኞች  ማለትም በቁጥር 12.500 የሚሆኑ  እና የሼር ኢትዮጵያ ት/ቤት -ተማሪዎች  እንዲሁ ወደ 6.500 የሚደርሱ በሙሉ ነፃ የህክምና አገልግሎት ያገኛሉ። የአካባቢዉ ማህበረሰብ  ደግሞ በዝቅተኛ ዋጋ የሚገለገሉ  ሲሆን ይህም ሆስፒታሉ  በየዓመቱ ከ100,000 በላይ ታካሚዎችን   እንደሚያክም ተገልጻል፡፡

Overview News

የሼር ፌርትሬድ ፕሪሚየም ኮሚቴ 16 አዲስ አፓርታማዎችን አስረከበ

20 October 2022 Aswin Endeman

በ2015 አዲስ ዓመት በወረሃ መስከረም የሼር ኢትዮጵያ ፕሪሚየም ኮሚቴ በባቱ /ዝዋይ/ ከተማ የሚገኙ አሮጌ እና እጅግ ተበሳቁለዉ የነበሩ16 የመኖሪያ ክፍሎች አፍርሶ እንደ አዲስ በመገንባት ከዚያም ቀደም ሲል በአሮጌዉና እጅጉን በተበሳቆለዉ ቤት ዉስጥ ሲኖሩ ለነበሩት ነዋሪዎች አስረክቧል፡፡ ከ 16 መኖሪያ ቤቶቹ ባሻገር የጋራ የሆኑ 2 ኩሽና እና 6 የወንድ አና የሴት መታጠቢያ ቤቶች ተገንብተዉ ለነዋሪዎቹ ተሰጥተዋል፡፡ይህም ፕሮጀክት ተጀምሮ የነበረዉ ከዛሬ 18 ወር አካባቢ ሲሆን በሼር ፌርትሬድ ፕሪሚየም ኮሚቴ  ከፌርትሬድ አበቦች ሽያጭ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ተደርጎለት የተሰራ ሲሆን ፣  እነዚህም 16ቱ  የመኖሪያ ክፍሎች አረጋውያን እና አካል ጉዳተኞች ያካተተ ሲሆን ለነዚህም ነዋሪዎች ጥሩ መኖሪያ ቤት እና ንፁህ የንፅህና መጠበቂያ ክፍሎች በማሟላት ጤናማ የመኖሪያ አካባቢ እንዲኖራቸዉ አድጓል።

ሼር ኢትዮጵያም እንደ አንድ አጋር ድርጅት የሁሉንም የጉልበት እና የሙያ ሰራተኞችን ወጪ በመሸፈን  ለፕሮጀክቱ መሳካት የራሱን አስተዋጽኦ አበርክቷል። የቤቶቹ የርክክብ ሂደትም የባቱ /ዝዋይ/ ከተማ ከንቲባ አቶ ገዛኸኝ ደጀኔ እና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የፌርትሬድ አፍሪካ ተወካይ አቶ ቦኒፌስ ሉዋንዳ በተገኙበት  ለነባር ነዋሪዎች ተላልፈዋል።  ለዚህ ፕሮጀክት  መሳካት ኮሚቴዉን እና ለሌሎች አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት በጠቅላላ ላቅ ያለ ምስጋና ለማቅረብ እንወዳለን።

Overview News

በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች የተደረገ የምግብ እርዳታ

7 October 2022 Aswin Endeman

ባለፈው አንድ አመት በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች በዝናብ እጥረት ምክንያት የተጎዱ  እንዲሁም የወደሙ ሰብሎች እና ለሞት የተዳረጉ እንስሳት እንዳሉ አንዳንድ መረጃዎች  ይጠቁማሉ። በዝዋይ እንዲሁም በአዳሜ ቱሉ ዙሪያ ከተጎዱ አካባቢዎች ዉስጥ የተወሰኑትን ለመደገፍ ያህል ሼር ኢትዮጵያ ወደ 800 ለሚጠጉ አባወራዎችን ለእያንዳንዳቸዉ 25 ኪሎ ግራም የበቆሎ ዱቄት ድጋፍ አድርጓል። ይህንንም በሼር ኢትዮጵያ ማኔጅመንት ስም ለአዳሚ ቱሉ ጂዶ ኮምቦልቻ ወረዳ አስተዳደር አስረክቧል። ስርጭቱም በተመሳሳይ የርክክቡ እለት መካሄዱን የድርጅቱ የህዝብ  ግንኙነት ስራ አስኪያጅ አቶ አማን ሙዳ ገልጸዋል።

 

 

Overview News

በቆቃ ለሚገኙ ተማሪዎች የተደረገ የመማሪያ ቁሳቁሶች ድጋፍ

30 September 2022 Aswin Endeman

ቀጣይነት ባለዉ ሁኔታ በቆቃ የሚገኝ የህዝብ ትምህርት ቤትን እንደምንደግፍ ይታወቃል  በቅርቡ መጠነኛ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው 50 ተማሪዎች የትምህርት ቤት ቁሳቁስ  ፣ የቦራ ወረዳ አስተዳደር ፣ የትምህርት ጽ/ቤት እና የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት አመራሮች  በተገኙበት የሼር ኢትዮጵያ ለተማሪዎችና ለቤተሰቦቻቸው የመማሪያ ቁሳቁሶቹን አስረክበናል።

የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እንዳለ ዋሪሶ ሼር ኢትዮጵያ ለአካባቢው ማህበረሰብ እያደረገ ላለው ያልተቋረጠ ድጋፍ አመስግነው ለሁሉም ተማሪዎች መልካም የትምህርት ዘመን እንዲሆላቸዉ ተመኝተዋል።

Overview News

ለሼር አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አዲስ የከርሰ ምድር ውኃ አውጥተናል

14 September 2022 Aswin Endeman

ባለፈው ወር በዝዋይ በሚገኘው አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤታችን አዲስ የከርሰ ምድር ውኃ አውጥተናል። በ 72 ሜትር ጥልቀት ላይ ነው ውኃው ሊገኝ የቻለው። ቁፋሮውን ላደረገው ለክርስቲያን ሰርቪስ አገልግሎት ልማት ድርጅት ምስጋና ይግባውና ዛፎቻችንንና ተክሎቻችንን ውኃ ለማጠጣት እንዲሁም ለመጸዳጃ ቤቶቻችን ውኃ ለመጠቀም አንቸገርም ። በሼር ትምህርት ቤቶች ውስጥ እየተማሩ በሚገኙት በሁሉም 6500 ተማሪዎች ስም ክርስቲያን ሰርቪስ የልማት ድርጅትን እና በተለይ ደግሞ የአካባቢው የፕሮጄክት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ቹቻ ጎበናን ከልብ ማመስገን እንወዳለን። በሌሎችም ሶስቱ ትምህርት ቤቶቻችን ሌላ ሦስት የከርሰ ምድር ውኃ ጉድጓዶችን ለመቆፈር በዝግጅት ላይ ነን።

Overview News

ክፍት የሥራ ቦታ፦ የትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር

6 September 2022 Aswin Endeman

በአዳሚ ቱሉ ለሚገኘው የሼር ኢትዮጵያ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አወዳድረን መቅጠር እንፈልጋለን።

በጣም ጥሩ የሆነ ከሰው ጋ የመግባባትና የማደራጀትና የመምራት ችሎታ አለኝ ብለው ያምናሉ? ቡድንን ማስተባበርና መምራት ይችላሉ? ቢቻል በግል ወይም በሕዝብ ትምህርት ቤት ውስጥ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ቢያንስ የ 3 ዓመታት የሥራ ልምድ ያለውን ባለሙያ እንፈልጋለን። ከርስዎ የምንፈልገው ቁርጠኛ እንዲሆኑና ቀና አመለካከት ያልዎት እንዲሁም ተማሪዎቻችን ያላቸውን እምቅ ችሎታ እንዲያወጡት እንዲያግዟቸው ነው!

በያወጣነውን ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ ከተመለከቱ በኋላ በእነርሱ የድርጣቢያ (ዌብሳይት) በኩል እባክዎ ማመልከቻዎን ያስገቡ።