
Category Archives: News


ባለፈው ሳምንት በፌርትሬድ መርሃግብር ስር ባለው DONUTS program ፕሮግራም በኩል የተለያዩ የአካል ድጋፍ መስጫ መሳሪያዎችን ማግኘት የቻልን ሲሆን ከነዚህም ውስጥ መነጽር ፣ ክራንቾች፣ ምቹ ጫማዎች ፣ሰው ሰራሽ እግሮች ቁጥራቸው ከፍ ላለ ሰራተኞቻችን ማሰራጨት ችለናል።
ይህም ለ 4 ዓመታት የሚዘልቅ መርሃ ግብር ሲሆን ዓላማዎቹም የሥርዓተ ጾታ እኩልነት ፣ ወጣቶች እና ተጋላጭ የሆኑ ቡድኖችን እና በተለይም የአካል ጉዳተኞችን ማበርታት እና መደገፍ ናቸው። ከዚህ በተጨማሪ መርሃግብሩ የፌርትሬድ ምርት አምራች ድርጅቶችን አቅም እና የሠራተኛ ማህበራትንም አቅም ለማጎልበት ዓላማ ያለው ፕሮግራም ሲሆን በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል የገንዘብ ድጋፍም ተደርጎለታል።
ሼር ኢትዮጵያ አካል ጉዳተኛ ሠራተኞችን ማካተት ሁል ጊዜ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው፣ ስለዚህም የ DONUTS ፕሮግራም ለ108 የአካል ጉዳተኛ ሠራተኞቻችን በመሳሪያ በመደገፉ ከፍ ያለ ምስጋናችንን ለማቅረብ እንወዳለን።
በዚህ ፕሮጀክት ሼር ኢትዮጵያ እና ፌርትሬድ አፍሪካ ከ ግራር ቤት ተሃድሶ ማህበር ጋር ተባብረዋል ማህበሩም የተጠየቀውን የመሣሪያ አይነት እና መሳሪያዎቹም በትክክለኛ ሁኔታ መገጣጠም እንዲችሉ ለመወሰን ይረዳ ዘንድ ለተጠቃሚዎች ልኬቶችን በቅድሚያ አከናውኗል በዚህም መሰረት ቀደም ተብሎ የተጠቀሱት ክራንቾች ፣ ሰው ሰራሽ እግሮች ፣ ምቹ ጫማዎች መነጽር እና መስማት የሚያስቸሉ መሣሪያዎችን ለ108 ሠራተኞቻችን ማዳረስ በመቻላችን እናም እነሱም በምቹ ሁኔታ መኖር እና መሥራት መቻላቸውን በማየታችን ደስተኞች ነን። ለተከበሩ አጋሮቻችንም የላቀ ምስጋናችንን በድጋሚ እናቀርባለን።

እ.ኤ.አ. መስከረም 5 በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎች አከባቢያቸውን ከቆሻሻ ለማፅዳት ኃይላቸውን አጠናክረው የሚቀሳቀሱበት የጽዳት ቀን ነው። በሼር ኢትዮጵያም በተለምዶ በየሦስት ወሩ ይህ የጽዳት ዘመቻ የሚከናወን ሲሆን በአዲሚ ቱሉ እና በቆቃ እርሻዎቻችንን ላይም እንዲሁ አከባቢን ለማፅዳት በንቃት እንሳተፍለን።
በባቱ /ዝዋይ በሚገኘው እርሻችን ደግሞ ከጎረቤት እርሻዎች ጋር በመቀናጀት እና ሃይልን በማስተባበር በጥቅሉ ከ 100 በላይ የሼር ኢትዮጵያ ሠራተኞች በየ ሶስት ወሩ በእነዚህ የጽዳት ዘመቻዎች ላይ ይሳተፋሉ።
ጥቃቅን ቆሻሻን ማየት ደስ የማያሰኝ ብቻ ሳይሆን አካባቢውን ይበክልና ወደ ወንዞች ፣ ሐይቆች እና ውቅያኖሶች ይጎዛል በመጨረሻም ስነ ምህዳሩንም ፣ፕላኔቷንም አደጋ ላይ ይጥልና ጤናችንን የሚጎዳ ይሆናል።
በዓመት አንድ ጊዜ ማፅዳት ብቻ ሳይሆን በየሩብ ዓመቱ ሁሉ በትጋት የሚሰሩ ሰራተኞቻችንን እና በጎ ፈቃደኞቻችን ማመስገን እንወዳለን በዚህም መሰረት በመስከረም 5 የዓለም የጽዳት ቀንን ስለምናከብር ሁሉም ሰው ኃይሉን ሰብስቦ እንዲቀላቀለን ጥሪያችንን እናቀርባለን።

የአየር ንብረት ለውጥን እና የደን ጭፍጨፋን ለመግታት ያቀደው አረንጓዴ አሻራ ዘመቻ ቀድም ሲል በሀገሪቱ ከ6 ዕመታት በፊት የተጀመረ ሲሆን እስካሁን ድረስ በመላው ኢትዮጵያ 3.7 ቢሊዮን በላይ ችግኞች እንደተተከሉ ይነገራል።. በዚህም መሰረት በየዓመቱ ለዘመቻው አስተዋፅኦ የምናደርግ ሲሆን በዚህም ዕመት በሐምሌ ወር የሥራ ባልደረቦቻችን በወርጃ እና በቃሞ ገርቢ ጋራዎች ላይ ከ 46.000 በላይ ችግኞችን በመትከል ተሳትፈዋል፣ ይህንንም በአከባቢው የአስተዳደር ጽ/ቤት ፣ በአከባቢው ባለሀብቶች እና በማህበረሰቡ ትልቅ ትብብር ማሳካት ተችሏል።
በተጠበቁ አካባቢዎች ችግኞችን ከመትከል በተጨማሪ በ 4ቱ የሼር ት/ቤቶችም ጊቢ ውስጥ 300 የፍራፍሬ ተሸካሚ ዛፎችን እና 1.000 ሌሎች ችግኞችን ተክለናል። በጥቅሉ በዘመቻው የተሳተፉትን የሥራ ባልደረቦቻችን እና በጎ ፈቃደኞችን ሁሉ ለማመስገን እንወዳለን።

በደች ፍላወር ፋውንዴሽን እና በአፍሪፍሎራ ለጋስነት በዝዋይ በሚገኘው ሼር ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ ሁለት አዲስ የኢ-መማሪያ ማዕከላትን ማቋቋም ችለናል።
ካማራ ኤዱኬሽን 50 አዳዲስ ኮምፒውተሮችን እና ሁለት ሰርቨሮችን የተከለ ሲሆን ፣ ኮምፒውተሮችን ለት/ቤት የሚያቀርብ እንዲሁም መምህራንን እያሠለጠነ፣ በገጠር እና ሩቅ በሆኑ የኢትዮጵያ ክፍሎች ለትምህርት ምቹ የሆኑ የኮምፒዩተር ክፍሎችን በማቋቋምና አስተማማኝ እንዲሁም ከወረቀት እና ከአቧራ-ነጻ አካባቢን በመፍጠር ያግዛል።
አሰልጣኞችም ለአንድ ሳምንት ያህል በሼር ኢትዮጵያ ትምህርት ቤት ተገኝተው 26 መምህራንን የኮምፒዩተር አጠቃቀም በስርአተ ትምህርቱ መሰረት በማሰልጠን እና በመሰረታዊ ጥገና ላይ ምክር ሰጥተዋል።
የካማራ ኮምፒውተሮች በኡቡንቱ ክፍት ምንጭ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ላይ ይሰራሉ። ከቀላል እስከ ልዩ የካማራ መማሪያ ስቱዲዮ ግብአቶችን ለሂሳብ እና ለሳይንስ የተለያዩ ትምህርታዊ ሶፍትዌሮች ተጭነዋል። ብሎም ኮምፒውተሮቹ እንዲሁ ከመስመር ውጭ የሆነው ዊኪፔዲያም ተጭኖላቸዋል፣ ይህም ውስን የበይነመረብ ግንኙነት ላላቸው ትምህርት ቤቶች ያልተለመደ የመማሪያ ምንጭ ይፈጥራል። ከሁሉም በላይ ደግሞ ኮምፒውተሮቹ በፒዲኤፍ የተጫኑ የትምህርት ሚኒስቴር የመማሪያ መጽሃፍቶች አጠቃላይ የትምህርት ቤቱን ሥርዓተ ትምህርት ያካተቱ ናቸው። በብዙዎቹ የኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች 40,000 ለሚጠጉ የመማሪያ መጽሀፍት አቅርቦት በጣም ውስን በመሆኑ ይህ ብቻውን ጥሩ ግብአት ይሆናል።
የደች ፍላወር ፋውንዴሽን የተቸገሩ ሰዎችን እና በተለይም የህጻናትን የኑሮ ሁኔታ እና ደህንነት ለማሻሻል ያለመ ነው። የደች ፍላወር ቡድን (DFG) አጋሮቹ በተገኙበት ቦታ የማህበረሰብ ፕሮጀክቶች ላይ በማተኮር የሚሰራ ነው። ቡድኑም /DFG ለምንኖርበት አለም ያለውን ሀላፊነት እየተወጣ ይገኛል።
በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችም በዚህ ተጠቃሚ ይሆናሉ ይላሉ የሼር ትምህርት ቤት ዳይሬክተር አቶ ንጉሴ አጋ፡ የኮምፒውተር ችሎታ ለተማሪዎቻችን እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። ሼር-ትምህርት ቤት በኢትዮጵያ ጥሩ ስም ካላቸው ት/ቤቶች ውስጥ አንዱ ነው። ሁሉም ተማሪዎች ማለት ይቻላል ዩኒቨርሲቲ ለመግባት ብቁ ይሆናሉ። አዳዲሶቹ የኮምፒውተር ክፍሎቸም ስማችንን ብሎም ደረጃችንን እንድናስጠብቅ እና ዲጂታል አለምን ለተማሪዎቻችን እንድንከፍት ያስችሉናል።
አፍሪፍሎራ በኢትዮጵያ ውስጥ ሼር ኢትዮጵያ በሚል ስም ሶስት እርሻዎች አለው። በሼር ትምህርት ቤቶች 6800 ልጆች ከመዋዕለ ሕፃናት እስከ ሁለተኛ ደረጃ ድረስ ትምህርት በነፃ ያገኛሉ።
ደች ፍላወር ግሩፕ እና ካማራ በዚህ ፕሮጀክት ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላቅ ያለ አድናቆት ያለን ሲሆን በተማሪዎቹ እና በመምህራን ስም ከልብ ለመምስገን እንወዳለን።

በኢትዮጵያ የግር ኳስ ፌደሬሽን አመራርነት ከተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች ተዉጣጥተው በምድብ C ተከፍለዉ ወደ ሼር ኢትዮጵያ እስታዲየም ተልከዉ የነበሩ 13 ቡድኖች ለተከታታይ ሁለት ወራት ሲያካሂዱ የነበረዉን የስልጠና እና የጨዋታ መርሃግብር ያለምንም የእስታዲየም ወጪ አጠናቀው ባሳለፍነው ሳምንት ወደ መጡበት ተመልሰዋል፡፡
በፍፃሜው ጨዋታም የካ ክፍለ ከተማ ከአዲስ አበባ እና ሀበሪቾ ከደቡብ ክልል ሀዲያ ዞን ተጋጥመው ሀበሪቾ 1-0 አሸንፏል። አሸናፊዎቹን እንኳን ደስ አላችሁ እያልን በስታዲየማችን በርካታ ተመልካቾች እና ደጋፊዎቻቸው ብዙ አጓጊ ጨዋታዎችን በመመልከት በመቻላቸው ደስተኞች ነን።
ሼር ኢትዮጵያ ለመረሃግብሩ መሳካት ሲያበረክት ለነበረዉ አስተዋፅኦ በፌደሬሽኑ እና በስፖርት ማህበረሰቡ ግንዛቤ ውስጥ በመግባቱና ይህንንም ማረጋገጥ ያስቸል ዘንድ የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል፡፡

ቅዳሜ ግንቦት 12 /2015 ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተጋበዙ የሆርቲካልቸር እና የዕፅዋት ሳይንስ ተማሪዎችን እንዲሁም መምህራንን አስተናግደናል። አቀባበል ከተደረገላቸዉም በኋላ ስለ እርሻዉ እንቅስቃሴ አጭር መግቢያ ተሰጥቷል በዚህም ላይ የኩባንያው CSR ተግባራትም ተብራርተዋል. በመቀጠልም የግሪን ሃውስ፣ የደረጃ አሰጣጥ፣ የዌት ላንድ እና የመስክ ጉብኝት ተካሂዷል።
ኩባንያው አካባቢያዊ እና ማህበራዊ መስተጋብሩን ተግባራዊ በሆነ መልኩ ለማሳየት ጥሩ አጋጣሚ የፈጠረለት ነበር፡፡. በመጨረሻም ተሳታፊዎቹ ሼር ኢትዮጵያ በማህበራዊ አገልግሎትና በአካባቢ ጥበቃ ላይ እያስመዘገበ ያለው ልማት እንዳስደነቃቸው ገልፀዋል።
እነዚህ ተማሪዎች በኢትዮጵያ በአበባ፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ዘርፍ ብሩህ ተስፋን ለመገንባት ትልቅ ሚና እንደሚጫወቱ ተስፋ እያደረግን ይህንን ዝግጅት በማቀዱና በማዘጋጀቱ EHPEAን እናመሰግናለን።

ባለፈው አመት በቦረና ዞን ድርቅ ተከስቶ ለሰብል ውድመት እና ለከብቶች ሞት ምክንያት ሆኗል ። ይህም በዘንድሮው አመትም በድጋሚ በመከሰቱ ህዝቡን ለመደገፍ ሀገር አቀፍ ዘመቻ ተጀምሯል። ሼር ኢትዮጵያም ዘመቻውን በመቀላቀል 13 ቶን የበቆሎ ዱቄት ገዝቶ ፣ አርብ መጋቢት 29 ለባቱ/ዝዋይ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት እና የተወሰኑ ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ርክክብ ተፈጽሟል ። እነሱም የተረክቡትነ የምግብ እህል በወቅቱ ለተጠቃሚዎች እንደሚያደርሱ ቃል ገብተዋል።



ከመጋቢት 12__15 / 2015 በፌርትሬድ የተመዘገቡ እርሻዎች ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በዱኩንዴ ካዋ ሙሳሳ የቡና እርሻ በኪጋሊ ሩዋንዳ አንድ ላይ አክብረዋል። ተሳታፊዎቹ ከኬንያ፣ ታንዛኒያ፣ ኮንጎ፣ ኡጋንዳ እና ኢትዮጵያ የተውጣጡ ነበሩ። ሼር ኤትዮጵያን በመወከልም ወ/ት ሕሊና ደበበ መኮንን የመረሃ ግብሩ ተሳታፊ ነበረች ።
ቡድኑ እንደ ዱኩንዴ ካዋ ሙሳሳ ኪጋሊ አቅራቢያ የሚገኘውን የቡና እርሻ የመሳሰሉ በርካታ ኩባኛዎችን ጎብኝቷል። እ.ኢ.አ በ2003 የተመሰረተው ይህ ኮፕሬቲፍ ከ300 ቡና አብቃይ ገበሬዎች ወደ 2,000 በላይ አድጓል። ሰማንያ በመቶው የዱኩንዴ ካዋ አባላት ሴቶች ሲሆኑ። ቡናቸውንም ”በሴቶች የመረተ ቡና ” ብለው ለገበያ ያቀርባሉ። ፌርትራድ ፕሪሚየም በመጠቀም ለህፃናት ትምህርት እና ማህበረሰቡን በቀጥታ የሚደግፉ ፕሮጀክቶችን ለምሳሌ እንደ ልብስ ስፌት ያሉ ለአካባቢው ገበያ እንደገና ጥቅም ላይ የሚውሉ የንፅህና መጠበቂያ ፓድዎችን የሚያመርት ነው። በካጄራ የህብረት ስራ ዩኒየን ሴቶችና ወጣቶች በሳሙና አመራረት እና በንብ ማነብ ላይ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል።
በእርሻችን እና በማህበረሰባችን ውስጥ የሴቶችን ሚና እና አቋም ማስከበር ለተለያዩ እና አካታች የሰው ሃይል በምናደርገው ጥረት ወሳኝ ግብ ነው። ለሰራተኞቻችን እና ለእዚህ አላማ አስተዋፅኦ ለሚያደርጉ የማህበረሰብ አባላት የተለያዩ ፕሮግራሞችን እና የስልጠና ኮርሶችን መስጠቱን እንቀጥላለን፣ በአለምአቀፍ ሁኔታ ከሌሎች እርሻዎች ለመማር እድል ስለሰጠን ፌርትሬድን ልናመሰግነው እንፈልጋለን በማለት ፕሮግራማቸውን አጠናቀዋል።

በቅርቡ ለሁለተኛ ዙር ጌሪት እና ኔል ባርንሆርን ስኮላርሺፕ ለአራት የሼር-ትምህርት ቤት ተማሪዎቸ ተሰጥቷል። የባርንሆርን ቤተሰብ ሼር ኢትዮጵያ እርሻን ፣ ሆስፒታል ና ትምህርት ቤቶቹን የመሰረቱ ናቸው። በየአመቱ ለ4 ተማሪዎች በኢትዮጵያ በመረጡት ዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት ወጪን እና የኑሮ ውድነት ለመደገፈ ብሎም ለመሸፈን የሚረዳ ወርሃዊ ገንዘብ ይሰጣቸዋል። የስኮላርሺፑ ዋና ግብ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡና የተቸገሩ ተማሪዎችን ለመርዳት ያስበ ነው።
ተማሪዎቹም ጣሃ አቡ ጁላ፣ ተመስገን ሰለሞን ስጦታ፣ ደጀኔ ኢጃሮ ናኔሶ እና ሃና በላይሁን ድልነሳው ሲባሉ ሽልማታቸውን ከጌሪት እና ኔል ባርንሆርን ልጅ ከጆን ባርንሆርን እጅ ተቀብለዋል። ጆን ባርንሆርም ተማሪዎቹ ላለፉት 16 ዓመታት ላሳዩት ትጋት እና እንዲሁም የሼር ትምህርት ቤት መምህራንና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን በተማሪዉ ቤተሰብ ስም አመስግኗል።
ከሁሉም 12 ከፍል ካጠናቀቁ ተማሪዎቸ ዉስጥ 8 ተማሪዎች ለስኮላርሺፕ ታጭተው 4ቱ በመጭረሻዉ ማጣሪያ ተመርጠዋል። ሌሎቹ 4 ቶቹ ድገሞ እያነዳነዳችዉ የላፕቶፕ ሽልማት አግኝተዋል። ስነ ስርዓቱም የተማሪ ቤተሰቦች፣የሼር ኢትዮጵያ ስራ አስኪያጆች፣የማህበረሰብ ሽማግሌዎች፣የሼር ት/ቤት ሰራተኞች፣የወላጆች ኮሚቴ እና የትምህርት ጽ/ቤት አስተዳደሮች ፣ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በሼር ት/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ተካሂዷል።
አቶ ባርንሆርን እና ቤተሰባችው ባለፉት አመታት ለሼር ትምህርት ቤቶች እና ሆስፒታል ያላሰለሰ ድጋፍ ስላደረጉልን እያመሰገንን እነዚህ ተማሪዎች ሼር ኢትዮጵያ በዝዋይ እና አካባቢው ማህበረሰብ ላይ እያሳደረ ያለው አዎንታዊ ተጽእኖ እውነተኛ ምሳሌ መሆናቸው ለመግለፅ እንወዳልን። ሁሉም የ12ኛ ከፍል ፈተናን ላጠናቀቁ ተማሪዎቸ እንዲሁም በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎቸ ለተመደባቸዉ ተማሪዎች መልካም የተምህርት ጊዜን እንመኘላችሃልን።
በኢትዮጵያ የሚገኙ የሼር ትምህርት ቤቶች ከ6800 በላይ ተማሪዎችን በሶስት ቦታዎች ያስተምራሉ። ወደ 400 የሚጠጉ ህጻናት – ከ 4 አመት ጀምሮ – በየዓመቱ በሼር ትምህርት ቤቶች ምዝገባ ወይም ቅበላ የሚከናወን ሲሆን ይህም 50 % ከአካባቢው ማህበረሰብ ልጆች እና 50% ቱ ድገሞ ከሠራተኞች ልጆች ይሆናለ።