Category Archives: News

Overview News

ሆርቲፍሎራ ኤክስፖ

17 March 2023 Aswin Endeman
የሼር ኢትዮጵያ የኤክስፖ ማዕከል

ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ በተካሄደው 8ኛው የሆርቲፍሎራ ኤግዚቢሽን ላይ ሶስት አስደሳች  ቀናትን በታላቅ ደስታ መለስ ብለን ሰንመለከት፣ ኤግዚቢሽኑ የተከፈተዉ በግብርና ሚኒስትሩ ዶ/ር ግርማ አመንቴ ሲሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።

ለእኛ ኤግዚቢሽኑ ከብዙ  ፍላጎት ካላቸው አካላት ጋር ስለ እርሻዎቻችን እና ውብ ጽጌረዳዎቻችንን በዘላቂነት ስለምናመርትበት መንገድ ለመነጋገር ጥሩ አጋጣሚ የፈጠረ ነበር። ብሎም ስለ ብዙው የCSR ፕሮጄክቶቻችንና፣ የእንቦጭ አረምን ከሀይቁ ላይ ለማሰወገድ በሚደረገው ዘመቻ የአካባቢውን ሴቶች በማስልጠን የተለያዪ ዓይነት የእጅ ስራ ምርቶችን አረሙን በመጠቀም አምርተዉ ለገበያ እንዲያቀርቡ በማድረግ  የምናበረከተውን አስተዋጽኦ  ጨምሮ ለመግልጽ ችለናለ፡፡

በዚህ አመት የኤግዚቢሽኑ መሪ ቃሉ ዘላቂነትን ማረጋገጥ’ የሚል ነበር እና ከEHPEA  (Gold certificate Code of Conduct) and MPS (Hortifoot print Calculator) የተባሉ  ሽልማቶችንም በማግኘታቸን  እንኮራለን።

በአጠቃላይ የተሳካ  ኤግዚቢሽን ነበር  እና ሁሉንም ጎብኝዎቻችንን በዚሁ እጋጣሚ ለማመሰገን እንውዳለን።

የሼር ኢትዮጵያ የኤክስፖ ቦታ የሼር ኢትዮጵያ የኤክስፖ ማዕከል በሆርቲፍሎራ ኤክስፖ የሼር ኢትዮጵያ ዝግጅት የሼር ኢትዮጵያ EHPEA የምስክር ወረቀት በሆርቲፍሎራ ኤክስፖ ላይ የሼር ኢትዮጵያ ማዕከላዊ ዝግጅት Ekisipoo Hortifilora keessatti agarsiisa abboota qabeenyaa Sheer Ethiopia

Overview News

በአዳሚ ቱሉ ሼር አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አዲስ የዉሃ ጉድጓድ

24 February 2023 Aswin Endeman
የሼር ኢትዮጵያ ድርጅት ስብሰባ

ባለፈው ሳምንት በአዳሚ ቱሉ በሚገኘው የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤታችን የዉሃ ጉድጓድ ተቆፍሮ ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ዓመት 4 የመመሪያ ክፈሎች ግንባታ እንጀምራለን፡፡ ይህ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሼር መዋላ ህፃናት ትምህርት ቤት በጣም ቅርብ ነው። መዋለ ህፃናት አሁን 350 ተማሪዎች አሉት። ለአዲሱ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዝግጅት ተጀምሯል። የተጀመረዉ ከውሃ እና ኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ነዉ፡፡ ውሃ በ 77 ሜትር ጥልቀት ላይ ወጥቷል. ምስጋናችን ለክርስቲያን ሰርቪስ ኢንተርናሽናል; ትምህርት ቤቶቻችን በሚገኙባቸው ቦታዎች ሁሉ የውሃ አቅርቦትን ለማሻሻል እየረዱን ነዉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ዛፎችን እና ተክሎችን ለማጠጣት እና መጸዳጃ ቤቶችን ለማጠብ በቂ ውሃ አለን:: የጉድጓድ ውሃ በቧንቧ በኩል ለአካባቢው ማህበረሰብ አባላት በነፃ እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡ አዲሱ የሼር አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መገንባት በትምህርት፣ በስራ እድል እና በመሠረተ ልማት ብዙ የሚፈለገውን እድገት ያመጣል።

የሼር ኢትዮጵያ የውሃ ፕሮጀክት ዝግጅት የሼር ኢትዮጵያ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ የሼር ኢትዮጵያ የውሃ ፕሮጀክት ግንባታ የሼር ኢትዮጵያ የውሃ ጉድጓድ ስራ የሼር ኢትዮጵያ የውሃ ፕሮጀክት በአዳሚ ቱሉ ሼር ት/ቤት የውሃ ጉድጓድ ግንባታ

Overview News

ሼር ተማሪዎች ተሸለሙ

31 January 2023 Aswin Endeman
በሼር ኢትዮጵያ የተሸለሙ ተማሪዎች

በቅርቡ ከ8ኛ ክፍል ተማሪዎቻችን ሶስቱ በተለየ ችሎታ ግኝት እና በፈጠራ ውድድር ላይ ተሳትፈዋል፤ የተለየ ፈጠራ የተዘጋጀዉ በኦሮሚያ ትምህርት ጽ/ቤት ነዉ፡፡ ውድድሩ በክልል ደረጃ የነበረ ሲሆን “በኦሮሚያ ሴት ተማሪዎች ቀን”  ላይ ቀርቧል፡፡ ይህም ዝግጅት በአዲስ አበባ በኦሮሚያ ባህል ማዕከል ተካሄዷል።

በእጅ ጥበብ ዘርፍ ሄለን ዮሴፍ፣ ማህሌት ብርሃኑ እና ቀነኒቱ ተሾመ አሸናፊ ሆነዋል፡፡ እነሱም ሜዳሊያዎችን እና የምስክር ወረቀት አግኝተዋል፡፡ በእለቱ የጥበብ ስራዎቻቸውን በታዳሚ ፊት እንዲያቀርቡ እድል የተሰጣቸዉ ሲሆን በመምህር ሮቢቲ መንገሻ ታጅበው ነበር፡፡ በዓሉን ለማክበር በማግስቱ የወዳጅነት ፓርክን ለማየት ሄደዋል፡፡

ወደ ሼር ትምህር ቤት ከተመለሱ በኋላም ሴት ልጆች በትምህርት ቤቱ አስተዳደር እና በተማሪዎቻቸው የክብር አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ ሴት ልጆቻችን ጥሩ  ስራ ሰርተዋል፡፡

የሼር ኢትዮጵያ ተማሪዎች ሽልማት በሼር ኢትዮጵያ የተሸለሙ ተማሪዎች የሼር ኢትዮጵያ የሽልማት ስነ-ስርዓት Barattoota Sheerii qormaata fudhachaa jiran በሼር ትምህርት ቤት ተማሪዎች የሽልማት ስነ-ስርዓት ላይ ተሳታፊዎች በደስታ ሲያጨበጭቡ በሼር ትምህርት ቤት የተሸለሙ ተማሪዎች ከሽልማታቸው ጋር ቆመው

 

Overview News

አዲስ የስራ ማስታወቂያ፡ ፀሐፊ/ የአስተዳደር ረዳት

27 January 2023 Aswin Endeman

በአዲስ አበባ ለሚገኘዉ ጽ/ቤታችን ወጣትና የመስራት አቅም ያላት፣ እንግሊዝኛ ቋንቋን አቃልጥፋ የምትናገር ከዉጭ የማስመጣት ሂደትን የምትከታተል እና የየእለቱን የፀሐፊነት ስራ ኃላፊነት የምትወጣ ፀሐፊ/የአስተዳደር ረዳት መቅጠር እንፈልጋለን፡፡

Please click here to find more information.

 

 

Overview News

ሸር ትምህርት ቤት የአካባቢ ፅዳት ቀን

10 January 2023 Aswin Endeman
በሼር ትምህርት ቤት የአካባቢ ጽዳት ላይ የተሳተፉ ተማሪዎች

የሸር ትምህርት ቤት ተማሪዎች በዛሬው ቀን የትምህርት ቤታችውን አካባቢ በማፅዳት አኩርተውናል፡፡ ይህ የፅዳት ስራ በአካባቢ ጥበቃ ክለብ አስተባባሪነት፤ በአስተማሪዎች እና በተማሪዎቻችን በጎ ፍቃድ የፕላስቲክ እና የተለያዩ ደረቅ ቆሻሻ ለመሰብሰብ ተችሏል፡፡ እንደሚታወቀው እንደ ሀገር የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ስርዓታችን የተሸሻለ  አይደለም፡፡ አስተማሪዎች እና ተማሪዎቻችን ለመጭው ትውልድ የፀዳ አካባቢን ለመፍጠር መነሳሳታቸውን አሳይተውናል፡፡ ጥሩ ስራ ተማሪዎቻችን!

የሼር ትምህርት ቤት ተማሪዎች በአካባቢ ጽዳት ላይ ተሳትፎ ሲያደርጉ የሼር ትምህርት ቤት ተማሪዎች የአካባቢ ጽዳት በሚያካሂዱበት ወቅት

Overview News

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጉብኝት

15 December 2022 Aswin Endeman
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሼር ትምህርት ቤት ጉብኝት ላይ

በቅርብ ጊዜ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቡድን 48 መምህራንና ተማሪዎችን አስተነግደናል፡፡ ሠላምታችንን ካቀረብን በኋላ  ስላ ካምፓኒ እድገትና አሠራር አጭር መግለጫ አቅርበናል፡፡  እነሱም ስለ አከባቢ ጥበቃ እና ማህበራዊ ሥራዎችን ከፍተኛ ደሰታ እንዳተሰማቸው ገልጸዋል፡፡ ስለ ድርጅቱ ማህበራዊ ሓለፍነት ፣ ስትረቴጅና ፕሮጄከቶች በምሰተር (Mr) አስዊን እንድመን ተገልጾዋል፡፡ ከመግለጫና ዉይይት በኋላ  ግሪን ሀዉስ ፣ የምርት ማቀናባበሪያ ሥራ እና ስለ ሰዉ ሰራሽ ረግረግ የመስክ ጉብኝት ተደርገዋል፡፡ በመጨረሸም፤ ተሳታፍዎቹ የሼር እትዮጴያ፣ የልማት፣ ማህበራዊ አገልግሎት እና የአካባቢ ጥባቃ ሥራ እንዳተመሰጡ ገልጾዋል፡፡ በማጠቃለያም ቡድኑ ሼር ካምፓን ግዜዉን ሰጥቶአቸዉተ ከእነሱ ጋር ባደርገዉ ቆይታና ለተደርገለቸዉ አቀባበል ምሰጋናቸውን አቅርብዋል፡፡ እኛም ቡድኑ ስለ ድርጅታችን የተርደዉን ፍላጎት  ላለቸዉ ሰዎች እንድያከፍሉዋቸዉ አጽኖት ሰጥተን አስገንዝበናል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሼር ትምህርት ቤት ጉብኝት ላይ በሼር ትምህርት ቤት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጉብኝት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሼር ትምህርት ቤት ውስጥ በሼር ትምህርት ቤት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የቡድን ውይይት በሼር ትምህርት ቤት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስብሰባ

 

Overview News

ሜላ ለእሷ፡ ወጣት ልጃገረዶችን በዘላቂ የወር አበባ መፍትሄዎች መደገፍ

5 December 2022 Aswin Endeman
Girls attending Sher Ethiopia's Mela health education

ባሳለፍነው ሳምንትበሼር-ትምህርት ቤታችን ለሚገኙ ለ1300 ሴት ተማሪዎች ፡ መላ ለሷ የሚል መጠሪያ ያለው አዲስ ፕሮጀክት ጀምረናል። የፕሮጀክቱ መጠሪያም እንዲሆን የመረጥነው (መላ)የአማርኛ ትርጓሜያዊ ፍች መፍትሄ የሚል ትርጉም ኣለው። በአፍሪካ ውስጥ ለሚገኙ ለብዙ ወጣት ሴቶች እና ልጃገረዶችችግር የሆነውን በዋጋ ተመጣጣኝ የሆነየሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ምርቶች እጥረትየሚቀርፍ መፍትሄ ነው:

ለብዙ ሰዎች የወር አበባ ንፅህና ጥበቃ ምቹ አይደለም። በዓለም ለሚገኙ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ልጃገረዶች ደግሞ በትምህርት፣ በጤና፣ በራስ መተማመን እና በሰብዓዊ መብቶቻቸው ላይ እንቅፋት ይፈጥራል። ለሌሎች ብዙዎች ደግሞ የወር አበባ መጀመር ለትምህርትመስተጓጎል ምክንያት ሲሆን ይታያል።

መላ ለእሷ፥ለአካባቢ ተስማሚ እና ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ የወር አበባ ምርቶችን እና የወር አበባ ጤና አጠባበቅ ትምህርትን በመስጠት፣ የሴቶችን እና የልጃገረዶችን ህይወት ለመለወጥ ወጥኖ የተነሳ ኢትዮጵያዊ ማህበራዊ ድርጅት ነው። የሼር ትምህርት ቤቶች እና መላ ለእሷትብብር እና በኔዘርላንድ የአበባ ፋውንዴሽን እርዳታ እድሜያቸው ከ11 እስከ 18 ዓመት ላሉ 1300 ልጃገረዶች፥የወር አበባ ንፅህና መጠበቂያዎችን እርዳታ እናቀርባለን። ከንፅህና መጠበቂያዎቹ በተጨማሪ የባለሙያዎች ቡድን የሼር ትምህርት ቤት መምህራንን የሚያሰለጥን ሲሆን፣ ለ1300 ተማሪዎች ደግሞ በሴቶች ክበብ በኩል የወር አበባ ጤና አጠባበቅ ላይ ስልጠና ይሰጣል።

የመላለእሷ ቡድን ላደረጉት ትብብር ትልቅ የሆነ ምስጋና እናቀርባለን ፥በመቀጠል የሆላንድ አበባ ፋውንዴሽን ለዚህ ተግባር ላደረጉት ድጋፍ እና ለወደፊትምለዚህ ፕሮጀክት ቀጣይነት ያለው ድጋፍለማድረግ ላሳዩት ቁርጠኝነት ከልብ እናመሰግናለን። ወጣት ሴቶች እምቅ ችሎታቸውን እንዲጠቀሙ ክብራቸው የሚጠበቅበት መብታቸውንም የማይጣስበት ዓለም አንድ ላይ እንገንባ።

Sher Ethiopia keessatti shamarran barnoota irratti hirmaatan Sher Ethiopia keessatti shamarran mari'achaa jiran Sher Ethiopia keessatti shamarran kitaaba dubbisaa jiran Sher Ethiopia keessatti shamarran meeshaalee barnootaa qabatanii በሼር ትምህርት ቤት የሜላ ለእሷ ፕሮግራም ውይይት በሼር ትምህርት ቤት የሜላ ለእሷ ፕሮግራም ተሳታፊ በሼር ትምህርት ቤት የሜላ ለእሷ ፕሮግራም ስልጠና በሼር ትምህርት ቤት የሜላ ለእሷ ፕሮግራም ተሳታፊዎች

Overview News

የገበሬዎች የደን ቀን እና ብዝሃ ህይወት

3 December 2022 Aswin Endeman
የገበሬዎች የደን ቀን እና ብዝሃ ህይወት

እሁድ ህዳር 26 የአርሶ አደሮች የደን ቀን በወራጃ ካሞ ተራራ ተከብሯል። በዚህ ፕሮጀክት ከ IDH VOCDA እና ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመሆን የተራቆቱ መሬቶችን መልሶ ማልማት እና መልሶ ማቋቋም ላይ እናተኩራለን። ባለፉት 5 ዓመታት ውስጥ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ዛፎች ተክለዋል.

በበዓሉ ወቅት, በግምት ተገኝተው. 200 ሰዎች, የፕሮጀክቱ ስኬቶች ተከበረ. 200 ሄክታር መሬት ያንሰራራ፣ የብዝሀ ህይወትም ጨምሯል። ኘሮጀክቱ እንደሚያሳየው ማህበረሰቦች ከአካባቢ ጥበቃ ጋር በተገናኘ በግብርና፣ በደን ልማት እና በገቢ ማስገኛ ተግባራት እንደ ኦርጋኒክ ማር እና የሞሪንጋ ሳሙና አመራረት ተጠቃሚ ይሆናሉ።

በቅርቡ ተመራማሪዎች የታደሰውን አካባቢ ብዝሃ ሕይወት ለመገምገም የዳሰሳ ጥናት አካሂደዋል። ጥናታቸውም የወረጃ ጥቃቅን ይዞታ ቢያንስ 29 የዛፍና የቁጥቋጦ ዝርያዎች ተሰጥቷቸዋል። ይህ ጥቃቅን ይዞታ በእርሻ ማሳዎች ውስጥ ተበታትነው ከሚታዩት በአቅራቢያው ካሉት አከባቢዎች በበለጠ በዝርያ ልዩነት እና በብዛት የበለፀገ ያደርገዋል። ስለዚህ ወርጃ ማይክሮ-catchment ጠቃሚ ለሆኑ የዛፍ እና የቁጥቋጦ ዝርያዎች እንደ የጂን ገንዳ እና የዘር ክምችት ቦታ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል።

ምንም እንኳን በዚያ መሬት ላይ የሚገኙት የነፍሳት ብዛት ከፍተኛ ቢሆንም ልዩነታቸው በአንፃራዊነት ዝቅተኛ ነው ይህም የእጽዋት ሽፋን ዝቅተኛ በመሆኑ አካባቢውን መንከባከብ እና መትከልን ይጠይቃል።

በዳሰሳ ጥናቱ 99 የአእዋፍ ዝርያዎች ታይተዋል ከነዚህም 6 ቱ የአእዋፍ ዝርያዎች አስጊ ናቸው። በተለይም በአካባቢው የሚገኙት ሦስቱ የአሞራ ዝርያዎች ለከፋ አደጋ የተጋለጠ ሲሆን በአካባቢው ጥሩ ቁጥር ያላቸው ጎጆዎች ይገኛሉ። በፕሮጀክቱ ለመቀጠል እና ሁሉም ባለድርሻ አካላት እንዲሰለፉ ለማድረግ ተጨማሪ ምክንያት.

Farmers participating in Sher Ethiopia's biodiversity workshop Sher Ethiopia keessatti shamarran barnoota fudhachaa jiran Sher Ethiopia keessatti meeshaalee barnootaa agarsiifaman Sher Ethiopia keessatti shamarran barnoota keessatti hirmaatan Sher Ethiopia keessatti shamarran mari'achaa jiran Sher Ethiopia keessatti shamarran barnoota fudhachaa jiran Sher Ethiopia keessatti meeshaalee barnootaa agarsiifaman Sher Ethiopia keessatti shamarran barnoota keessatti hirmaatan Sher Ethiopia keessatti meeshaalee eegumsa fayyaa agarsiifaman

Overview News

አፍሪፍሎራ ሼር ፣ ቫን ዲጅክ ፍሎራ እና የኔዘርላንድ ፍላወር ፋውንዴሽን በጋራ በመሆን ለሼር ኢትዮጵያ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ወተት /እርጓ /የመመገብ ፕሮጀክትን አስጀመሩ።

26 October 2022 Aswin Endeman
በሼር ኢትዮጵያ ት/ቤት የወተት ፕሮግራም ተሳታፊ ተማሪዎች

ፕሮጀክቱም በዚህ የትምህርት ዘመን እድሜያቸዉ ከ4 እስከ 6 ዓመት የሚሆናቸው 1350 የሚሆኑ የሼር ኢትዮጲያ ትምህርት ቤቶች  ተማሪዎች በሳምንት ሁለት ጊዜ በጤናማ ንጥረ ነገሮች የበለጸገ የፕሮቲን እርጎ እንዲያገኙ ይረዳል። በአንድ ጊዜ የወተት ምገባ ለ አንድ የ5 አመት ልጅ ዕለታዊ የፕሮቲን ፍላጎት 33% እና 10% የቀን ካሎሪ ይሰጠዋል. እርጎው በየእለቱ ሁሉም ልጆች በትምህርት ቤት በሚያገኙት ትኩስ ምግብ ጋር አብሮ ይሰጣል ።

በፕሮጀክቱም ድጋፍ ልጆቹ የሚያስፈልጋቸውን የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ ያግዛል። በዚህ መንገድ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ስጋትን በመቀነስ የህጻናትን ትምህርት ተሳትፎ እንጨምር እናደርጋለን። ይህም ፕሮጀክት ከአስራ ስድስት ላላነሱ ሰዎች የሥራ እድል የሚሰጥ ሲሆን እንዲሁም ከሁለት በባቱ/ ዝዋይ / ውስጥ ከሚገኙ የወተት ተዋጽኦ አምራችና አቅራቢ ድርጅቶች ጋር የስራ ዉል ተፈራርመናል።

ከአጋሮቻችን ቫን ዲጅክ ፍሎራ እና የኔዘርላንድ ፍላወር ፋውንዴሽን ላደረጉልን ለዚህ ለጋስ እርዳታ በሁሉም የሼር ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች፣ ወላጆች እና አስተማሪዎች ስም እጅጉን የላቀ ምስጋና ልናቀርብላቸዉ እንወዳለን።

በሼር ኢትዮጵያ ት/ቤት የወተት ፕሮግራም ተሳታፊ ተማሪዎች በሼር ኢትዮጵያ ት/ቤት የወተት ፕሮግራም ተጠቃሚ ህፃን በሼር ኢትዮጵያ ት/ቤት የወተት ፕሮግራም ተሳታፊዎች በሼር ኢትዮጵያ የወተት ፕሮግራם ተጠቃሚ ተማሪዎች በሼር ኢትዮጵያ ት/ቤት ተማሪዎች የወተት ፕሮግራም ላይ በሼር ኢትዮጵያ ት/ቤት የወተት ስርጭት ሥነ-ሥርዓት በሼር ኢትዮጵያ ትምህርት ቤት ውስጥ ተማሪዎች ወተት እየተመገቡ Sheer fi Vaan diik Floraa garee hojii waliin mari'achaa jiru Sheer fi Vaan diik Floraa sagantaa leenjii gaggeessaa jiru Sheer fi Vaan diik Floraa barattoota waliin mari'achaa jiru Sheer fi Vaan diik Floraa bakka pirojeektii aananii mana baruumsaa keessatti hojjetaa jiru

Overview News

ሼር ኢትዮጵያ ሆስፒታል አዲስ የማደንዘዣ መስጫማሽን ግዢ አከናወነ፡፡

25 October 2022 Aswin Endeman
የሼር ኢትዮጵያ ሆስፒታል አዲስ መሳሪያ

በባቱ/ዝዋይ ከተማ የሚገኘው ሼር ኢትዮጵያ  ሆስፒታል አገልግሎቱን ለማሻሻል ባደረግነው ጥረት በቅርቡ አዲስ የማደንዘዣ መስጫማሽን ግዢ አከናዉኗል። የማደንዘዣ ሰጪ ባለሙያ የሆኑት ሲስተር ወርቄ አቦይ በሰጡት አስተያየት በማሽኑ አንድ ጊዜ ማደንዘዣዉን ለበሽተኛዉ ከተሰጠ በኃላ ሙሉ በሙሉ በራሱ  የሚሰራ በመሆኑ የማደንዘዣ ሰጪ ባለሙያዉ በሽተኛውን እየተከታተለ በቀዶ ጥገናው ስራ ላይ ተጨማሪ እርዳታን መስጠት ያስችለዋል ብለዋል።

ሌላው የአዲሱ ማሽን ጥቅም ደግሞ የሕፃናትን የቀዶ ጥገና ሕክምና  መስጠት የሚያስችል  መሆኑን የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ደምሳቸዉ ጌታቸዉ እንዲህ ሲሉ አብራርተዋል፡- ‘ከዚህ ቀደም ህጻናት ቀዶ ጥገና ሲያሰፈልጋቸዉ ወደ ሌሎች ሆስፒታሎች  የምንልክ የነበረ ሲሆን አሁን ግን አዲሱን ማሽን በመጠቀም ህክምናዉን በዚሁ በራሳችን ሆስፒታል መስጠት እንድንችል ያደርገናል ብለዋል፡፡

ማሽኑም በክፍሉ ከተተከለ እና  ለሚመለከታቸው ሁሉም የክፍሉ ሰራተኞች በአምራች ድርጅቱ ባለሙየዎች  ሙያዊ ስልጠና, ከተሰጠ በኃላ ሙሉ በሙሉ በስራ ላይ ይውሏል ፡፡

በሼር ኢትዮጵያ ሆስፒታል ሁሉም የሼር ሰራተኞች  ማለትም በቁጥር 12.500 የሚሆኑ  እና የሼር ኢትዮጵያ ት/ቤት -ተማሪዎች  እንዲሁ ወደ 6.500 የሚደርሱ በሙሉ ነፃ የህክምና አገልግሎት ያገኛሉ። የአካባቢዉ ማህበረሰብ  ደግሞ በዝቅተኛ ዋጋ የሚገለገሉ  ሲሆን ይህም ሆስፒታሉ  በየዓመቱ ከ100,000 በላይ ታካሚዎችን   እንደሚያክም ተገልጻል፡፡

በሼር ኢትዮጵያ ሆስፒታል የማደንዘዣ መሳሪያ ትውውቅ በሼር ኢትዮጵያ ሆስፒታል የማደንዘዣ መሳሪያ ስብሰባ በሼር ኢትዮጵያ ሆስፒታል አዲስ የማደንዘዣ መሳሪያ